Awramba Times Issue 171

March 10, 2018 | Author: Tigist Muluken | Category: N/A
Share Embed Donate


Short Description

Download Awramba Times Issue 171...

Description

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

በነፃ ገበያ ዙሪያ የሚነፍሰው

ኢትዮጵያውያኑ

የተሳሳተ አመለካከት

የተስፋ ፍሬዎች

በፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

በአለማየሁ ገ/ማርያም (ፕ/ር)

በ ገፅ 14 -15

4ኛ ዓመት ቁጥር 171

ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

ዋጋ 7፡00 ብር

ፎቶ በሲሳይ ጉዛይ

‹‹ወደዚህ የመጣሁበት ዋናው ምክንያትም ይኸው ነው። አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ስንዘጋጅ አሜሪካ ከጀርባችን መሆኗን ማረጋገጥ እንፈልጋለን። የእናንተ ድጋፍና ምክር ለእያንዳንዱ እንቅስቃሴአችን ወሳኝ ነው። … ኢትዮጵያውያን ነጻነት እና ዴሞክራሲ እንዲጎናጸፉ እንፈልጋለን። … ማርክሲስት - ሌኒኒስት አይደለንም። ነገሮችን በአዎንታዊ መንገድ እንድትገነዘቡልን እንፈልጋለን።››..... በዳዊት ከበደ.... በ ገፅ 3

የመለስና የ‹‹ሲ.አይ.ኤ››ው አባል ምስጢራዊ ውይይት የብተና ፖለቲካ

የብርቱካን የመኸር ጊዜ

የወለደው አዲስ ምዕራፍ!

አቶ አብርሃም ያየህ

የመንግስት ተቋማትን ገመና ያጋለጠው ሪፖርት

የትምህርት ሚኒስቴር የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብለት 1 ነጥብ 45 ቢሊዮን ብር ክፍያ ፈፅሟል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ያለአግባብ ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለጀነሬተር ኪራይ ከፍሏል የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሕገ-ወጥ መንገድ ብዛቱ አምስት ሺህ የሚሆን ጥራዝ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ አሳትሞ ሒሳብ ሰብስቧል

እርሳቸው “በኢትዮጵያ ከታዩ ሥርዓቶች ውስጥ ይህንን ሥርዓት በቀላሉ ማሸነፍ ይቻላል” ብለው ያምናሉ። የኢህአዴግ ህልውና የተመሰረተው በራሱ ጥንካሬ ላይ ሳይሆን በተቃዋሚዎች ድክመት እና ሕብረት ማጣት ላይ እንደሆነ ይገልፃሉ። አዎን፣ የዛሬ ትንታኔያቸው ማጠንጠኛ ብርቱካን ናት። ከፖለቲካው እርቃ ትቆያለች የሚል እምነት የላቸውም። “በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ አንዲት መልካም ፍሬ የምታፈራ የምታምር ድንቅ ዛፍ ተተክላ በጥሩ ሁኔታ በቅላለች፤ ብዙ ውሽንፍርና ውርጭ ተቋቁማ ፍክት ብላ አብባለች” በማለት ይተርኩና ሲደመድሙም፣ “እናም በፍሬው ለቀማ ላይ ወ/ሪት ብርቱኳን ቅርጫቷን ይዛ ብቅ አትልም ብሎ መጠርጠር የማይታሰብ ነው” ይሉናል።

በ ገፅ 11

የአሲድ ጥቃት የተፈፀመባት አረፈች

ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተመደበው ከፍተኛ ሀብት ለሌላ ዓላማ ውሏል። የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት ያጸደቀው በጀት የፋይናንስ አስተዳደር ሕጉን፣ ደንብና መመሪያ በሚፈቅደው መሠረት በትክክል ሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ በ2002 በጀት ዓመት ሒሳብ ላይ ባከናወነው ኦዲት በርካታ የሒሳብ አያያዝ ግድፈቶችን ማግኘቱንም አስታውቋል።

በ ገፅ 4

ሂላሪ ክሊንተን ሰኞ አዲስ አበባ ይገባሉ

የዩ.ኤስ አሜሪካን የውጭ ጉዳይ ሴክሬታሪ የሆኑት ሂላሪ ክሊንተን በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት ለማድረግ የፊታችን ሰኞ አዲስ አበባ እንደሚገቡ በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካን ኢምባሲ ለአውራምባ ታይምስ በላከው መግለጫ እስታወቀ፡፡ ሂላሪ ክሊንተን በሁለት ቀን ቆይታቸው በአፍሪካ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤት

በ ገፅ 19

ተገኝተው ንግግር የሚያደርጉ ሲሆን፣ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ ከሌሎች የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናትና የአፍሪካ ህብረት ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ፡፡ በአሜሪካ መንግሥት ድጋፍ የተቋቋሙ ፕሮጀክቶችንም ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በ ገፅ 19

በ ገፅ 21

‹‹የሠራዊት እና ሠራዊቱ ድራማ›› የኪነ-ጥበብ ‹‹ባለሙያዎች›› እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስብሰባ ቅሬታዎች በርክተውበታል

ለ20 ዓመታት ተፈትኖ የወደቀ አካል በቃህ ሊባል ይገባዋል! መውጫው መንገድ ፀንቶ መታገል ብቻ ነው! ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

ከሰሞኑ ‹‹የኢህአዴግ ደጋፊ አርቲስቶች ማኅበር›› ሳይቋቋም አይቀርም! ለመረጃ ቅርብ ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ ይሁኑ

2

ርዕሰ አንቀፅ

የካቲት 2000 ዓ.ም ተመሠረተ አውራምባ ታይምስ፡በብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ ኃላ/የተ/ የግል/ማህበር ስር የሚታተም፤ በፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር፤ በንግድ ሚኒስቴር በቁጥር 020/2/6572/2001 የተመዘገበ ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው፡፡ T’@Í=”Ó ›?Ç=}` Ç©ƒ ŸuÅ ª“ ›²ÒÏ õì
View more...

Comments

Copyright ©2017 KUPDF Inc.
SUPPORT KUPDF